የኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ-ሥርዐት እና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ ዳሰሳ

Authors

  • አንተናኔ ጥሩ ዘውዴ Author

Abstract

The author is triggered to write on this topic following taking part in a training focusing on the draft criminal procedure and evidence law. The draft come up with intriguing principles and concepts. The paper aims to compare and contrast the current Ethiopian criminal procedure law with the draft of criminal procedure and evidence law with the perspective of issues experienced in practice. One of the major objectives of the legislation is to ensure the respect for constitutionally guaranteed human rights in the process of criminal investigation, prosecution, trial and execution of judgment. Hence, the draft legislation recognized presumption of innocence, prohibition of double jeopardy and equality before the law. The draft has also introduced novel legal principles and mechanisms such as alternative dispute resolution, review of final judgment and international cooperation on criminal matter. While these changes are commendable, the author tried to pinpoint issues still to be fixed in relation to treatment of arrested persons, police investigation, remand and bail, preliminary inquiry, judications of courts and charges

የወንጀል ሥነ-ሥርዐት እና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ ስልጠና ስሳተፍ ረቂቁ ያስተዋወቃቸው የሕግ መርሆቸ እና በሕጉ የተቀመጡት አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦች ትኩረቴን ስቦታል። ይህም በ1954 ዓ.ም የወጣዉን እና እስከ አሁን በስራ ላይ ያለዉ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ (ከዚሕ በኋላ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ እንደ አስፈላጊነቱ የሚባለዉ) እና ይህን ሕግ ለማሻሻል የወጣዉ ረቂቅ የወንጀል ሥነ-ሥርዐት እና የማስረጃ ሕግ (ከዚሕ በኋላ ረ/የወ/ሥ/ሥ/ እና ማ/ሕ እንደ አስፈላጊነቱ የሚባለዉ) ጋር ምን ልዩነት እና አንድነት እንዳላቸው እንዲሁም በተግባር ከሚታዩ ችግሮች አንፃር እንድዳስስ አነሳስቶኛል፡፡ የረቂቁ ሕግ አንድ ዓላማ በወንጀል ምርመራ፣ ክስ፣ ፍርድ ሂደትና የውሳኔ አፈጻጸም ወቅት በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ የሰብዓዊ መብቶችን ማክበር እና ማስከበር ሲሆን ለዚህም ነፃ ሆኖ የመገመት መብት፣ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ክስ ስለመከልከሉ፣ በሕግ ፊት እኩል መሆን እና ሌሎች መሰረታዊ ጥበቃዎች በረቂቁ እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በተጨማሪም አማራጭ የሙግት መፍቻ፣ የመጨረሻ ፍርድን እንደገና ማየት፣ በወንጀል ጉዳዮች የዓለም አቀፍ ትብብርን አስፈላጊነት ከግምት አስገብቷል፡፡ ነገር ግን በወንጀል ስነስርዐት ውስጥ በተግባር የሚስተዋሉ ችግሮችን ማለትም የፖሊስ ምርምራ እና የተከሳሽ አያያዝ፣ በፖሊሰ ጣቢያ እና በማረሚያ ቤት የእስረኞች እንክብካቤ፣ ጊዜ ቀጠሮ እና ዋስትና፣ ቀዳሚ ምርመራ፣ የፍ/ቤቶች ሥረ ነገር ስልጣን፣ የዓ/ሕግ ክስ፣ የተከላካይ ጠበቃ አገልግሎት እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ረቂቅ ሕጉ ሊቀርፋቸው የሚገቡ ክፍተቶች በዚህ ፅእሁፍ ተነቅሰዋል፡፡

Author Biography

  • አንተናኔ ጥሩ ዘውዴ

     የህግ ድግሪውን ከቅድስተ-ማርያም ዩንቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ድግሪውን በEnvironmental and Land Law ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ ያገኘ ሲሆን  በአሁኑ ወቅት በምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት እየሰራ ይገኛል።

Downloads

Published

2024-11-17

How to Cite

የኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ-ሥርዐት እና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ ዳሰሳ. (2024). Choke Journal Of Law, 1(1). https://journal.waletsoftware.com/index.php/CJL/article/view/18